ኢዮብ 36:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራቸውንና መተላለፋቸውን ይነግራቸዋል፥ ብዙ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ ተግባራቸውን ይነግራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግባራቸውንና መተላለፋቸውን በትዕቢትም እንደሚሠሩም ይናገራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በትዕቢታቸው፥ የሠሩትን ኃጢአት ይገልጥባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥራቸውንና መተላለፋቸውን በትዕቢትም እንዳደረጉ ይናገራቸዋል። |
አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በነገረ ሠሪነታቸውም ይውደቁ፤ እንደ ሐሰታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ አቤቱ፥ እነርሱ አሳዝነውሃልና።
ዐመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኀጢአታችንም መስክሮብናልና፥ ዐመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድቅንም አላወቅንምና።
“ኀጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤