አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
ኢዮብ 31:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ መንገዴን የሚያይ አይደለምን? እርምጃዬንስ ሁሉ የሚቈጥር አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ መንገዴን አያይምን? ርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የማደርገውን ሁሉ አያይምን? እርምጃዎቼንስ አይቈጣጠርምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን? |
አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ዐይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፤ ለዘለዓለም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ በድል አድራጊነትም ያኖራቸዋል። እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።
ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው” አለ።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።