ኢዮብ 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥኣን ምክር ከእርሱ የራቀች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤታቸውን በመልካም ነገር የሞላው ግን እርሱ ነው፤ ስለዚህ ከኀጢአተኞች ምድር እርቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥ የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ቤታቸውን በብልጽግና የሞላው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኔ የክፉ ሰዎችን ሐሳብ አልቀበልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፥ የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። |
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥር ሰድደዋል፤ ወልደዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራን እየሠራ ከሰማይ ዝናምን፥ ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”