Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኀጢ​ኣ​ተኛ ብሆን በአ​ንተ ዘንድ መል​ካም ነውን? የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል ብለ​ሃ​ልና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምክር ተመ​ል​ክ​ተ​ሃ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ይህን ያኽል ማስጨነቅህ አግባብ ነውን? አንተ ራስህ የፈጠርከውን ሰው መናቅ ይገባሃልን? የክፉ ሰዎችስ ሤራ ደስ ያሰኝሃልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የኃጥአንንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 10:3
27 Referencias Cruzadas  

“እጆ​ችህ ፈጠ​ሩኝ፤ ሠሩ​ኝም፤ ከዚ​ያም በኋላ ዞረህ ጣል​ኸኝ።


በጠ​ራ​ኸ​ኝም ጊዜ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ነበር፤ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አት​ና​ቀኝ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቍጣ ትመ​ልስ ዘንድ፤ እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ ነገር ከአ​ፍህ ታወጣ ዘንድ፤


ዐይ​ኖ​ችን አፍ​ዝዞ ጋረ​ደኝ፤ በተ​ሳለ ጦርም ጕል​በ​ቴን ወግቶ ጣለኝ። በአ​ን​ድ​ነ​ትም ከበ​ቡኝ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥ መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።


“እነሆ፥ በጎ​ነ​ታ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ውስጥ አለች፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንን ሥራ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።


ነገር ግን ቤታ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም ነገር ሞላ፤ የኃ​ጥ​ኣን ምክር ከእ​ርሱ የራ​ቀች ናት።


“እን​ደ​ዚህ የፈ​ረ​ደ​ብኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ነፍ​ሴ​ንም መራራ ያደ​ረገ ሁሉን የሚ​ችል ሕያው አም​ላ​ክን!


ምሕ​ረት የሌ​ላ​ቸው ሰዎች ደበ​ደ​ቡኝ፥ የገ​ረ​ፈ​ችኝ እጅም በረ​ታች።


እኔን በማ​ኅ​ፀን የፈ​ጠረ እነ​ር​ሱ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን? በማ​ኅ​ፀ​ንስ ውስጥ የሠ​ራን አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፈጠ​ረኝ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ እስ​ት​ን​ፋስ ያስ​ተ​ም​ረ​ኛል።


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሁን ሰው አይ​ጥ​ለ​ውም፥ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ች​ንም እጅ አያ​በ​ረ​ታም። የዝ​ን​ጉ​ዎ​ች​ንም መባ አይ​ቀ​በ​ልም።


“ስለ​ዚህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ታላ​ቁና ኀያሉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን ይል​ካል።


በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?


በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤ ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።


ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ጥል​ቁም ብወ​ርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤


አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን።


ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos