እነሆ፥ በዘለፋ እደክማለሁ፤ አልናገርምም፤ አሰምቼም እጮኻለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለኝም።
“ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።
እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ ድረሱልኝ ብዬ ብጣራ ፍርድ የለኝም።
ተበደልኩ ብዬ ብጮኽ የሚሰማኝ አላገኘሁም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ አቤቱታ ባሰማም ፍትሕ አላገኘሁም።
እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ አሰምቼም ብጠራ ፍርድ የለኝም።
ኀጢኣተኛ ብሆን በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? የእጅህን ሥራ ቸል ብለሃልና፤ የኃጥኣንንም ምክር ተመልክተሃልና።
ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥ ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ።
እነሆ፥ ደፍራችሁ፥ በእኔ ላይ በጠላትነት እንደ ተነሣችሁ ዐውቄአለሁ።
ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልሰማኸኝምም፤ እነርሱ ግን ቆመው ተመለከቱኝ።
እኔ ራሴ ልታነቅ በወደድሁ ነበር ይህም ባይሆን ሌላው እንዲሁ እንዲያደርግልኝ እለምናለሁ።
በጠባቡ ሄድሁ፥ የሚያሰፋልኝም አጣሁ፥ በጉባኤም መካከል ቆሜ እጮኻለሁ።
ኢዮብ እንዲህ ብሎአልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርዴን አስወገደ፤
ወይም ፍርዴን መቃወምህን ተው፥ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን?
በኃጥኣን እጅ ተሰጥተዋልና፤ የምድር ፈራጆችን ፊት ይሸፍናል፤ እርሱ ካልሆነ ማን ነው?
የሚከራከረኝ ሰው ቢሆን ኖሮ፥ ወደ አደባባይ በአንድነት በሄድን ነበር!
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ።
ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠራለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።
በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከለከለ።