Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣ እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ ይህንን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ሌላ ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ምድር በክፉ ሰዎች እጅ ተላልፋ ስትሰጥ እርሱ የዳኞችን ዐይን ይሸፍናል፤ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ካልሆነ ታዲያ፥ ማነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ እርሱ ካልሆነ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:24
24 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት ወጣ፤ ሲወ​ጣም ያለ​ቅስ ነበር፤ ራሱ​ንም ተከ​ና​ንቦ ነበር፤ ያለ​ጫ​ማም ይሄድ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተከ​ና​ን​በው ነበር፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም ይወጡ ነበር።


ንጉ​ሡም ፊቱን ሸፈነ፤ ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ድምፅ፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ” እያለ ይጮህ ነበር።


ኀጢ​ኣ​ተኛ ብሆን በአ​ንተ ዘንድ መል​ካም ነውን? የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል ብለ​ሃ​ልና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምክር ተመ​ል​ክ​ተ​ሃ​ልና።


መካ​ሮ​ች​ንም እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ች​ንም አላ​ዋ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


ዐይ​ኖ​ችን አፍ​ዝዞ ጋረ​ደኝ፤ በተ​ሳለ ጦርም ጕል​በ​ቴን ወግቶ ጣለኝ። በአ​ን​ድ​ነ​ትም ከበ​ቡኝ።


እነሆ፥ በዘ​ለፋ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ አል​ና​ገ​ር​ምም፤ አሰ​ም​ቼም እጮ​ኻ​ለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለ​ኝም።


ፊታ​ቸ​ውን አይ​ተህ ያደ​ነ​ቅ​ሃ​ቸው አሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ ድሆ​ችን በዐ​መፅ ጠላህ


ድሆ​ችን ከከ​ተ​ማ​ውና ከገዛ ቤቶ​ቻ​ቸው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው የሕ​ፃ​ና​ት​ንም ነፍስ እጅግ አስ​ጮሁ፤


እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ሐሰ​ተኛ ነህ የሚ​ለኝ፥ ነገ​ሬ​ንስ እንደ ኢም​ንት የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው?”


ከአ​ው​ስ​ጢድ ሀገር ከአ​ራም ወገን የሆነ የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤሊ​ዩስ ተቈጣ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና ኢዮ​ብን ተቈ​ጣው።


ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም።


በም​ድር ላይ አል​ዘ​ነ​በ​ምና መሬቱ ስን​ጥ​ቅ​ጥቅ ስለ ሆነ አራ​ሾች ዐፈሩ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos