ኢዮብ 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃኑ በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፤ መብራቱም በላዩ ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድንኳኑ ብርሃን ይጨልማል፤ መብራቱም በላዩ ይጠፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥ መብራቱም በላዩ ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ድንኳን ውስጥ ያለው መብራት ይጠፋል፤ ብርሃኑም ይጨልማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥ መብራቱም በላዩ ይጠፋል። |
በጠፋህም ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብትንም አጨልማለሁ፤ ፀሐዩንም በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም።
የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”