ኢዮብ 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፤ ፍሬውም ከላዩ ይረግፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥሩ ከታች ይደርቃል፤ ቅርንጫፉም ከላይ ይረግፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥሩ ከመሠረቱ እንደሚደርቅና ቅርንጫፎቹም እንደሚረግፉ ዛፍ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል። |
ንጹሕ እንዳልሆነና በደም እንደ ረከሰ ልብስ አንተም ንጹሕ አይደለህም። ምድሬን አጥፍተሃልና፥ ሕዝቤንም ገድለሃልና ክፉ ዘር አንተ እንግዲህ ለዘለዓለም አትኖርም።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።