እኔ እዋሳለሁ፤ ከእጄ ትሻዋለህ፤ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁህ ልሁን።
ኢዮብ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ጋር አጋና የሚማታ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላክ ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እባክህን፥ አንተ ዋስ ሁነኝ፥ ለእኔ ተያዥ የሚሆነኝ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ከአንተ በቀር ለእኔ የሚቆምልኝ የለምና አንተው ራስህ ተያዥ ሁነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ፥ ከእኔ ጋር አጋና የሚመታ ማን ነው? |
እኔ እዋሳለሁ፤ ከእጄ ትሻዋለህ፤ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁህ ልሁን።
እኔ አገልጋይህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዬ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ መልሼ በፊትህ ባላቆመው በአባቴ ዘንድ በዘመናት ሁሉ ኀጢአተኛ እሆናለሁ።
እንግዲህ ድህነት እንደ ክፉ መልእክተኛ፥ ችግርም እንደ ደኅና ርዋጭ ይመጣብሃል። ሰነፍ ባትሆን ግን ባለጸግነትህ እንደምንጭ ይመጣልሃል፤ ችግርም እንደ ክፉ ርዋጭ ከአንተ ይርቃል።