ኢዮብ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዦሮ ነገርን የሚለይ አይደለምን? ጕረሮስ መብልን የሚቀምስ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፥ ጆሮም የቃላትን እውነት ይለይ የለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምላስ የምግብን ጣዕም ለይቶ እንደሚያውቅ፥ ጆሮም የንግግርን ዐይነት መርምሮ ይለያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምላስ መብልን እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃልን የሚለይ አይደለምን? |
የሚሻለውን ሥራ እንድትመረምሩና እንድትፈትኑ፥ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ያለ ዕንቅፋት ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፦