ኢዮብ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢኣተኛ ብሆን በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? የእጅህን ሥራ ቸል ብለሃልና፤ የኃጥኣንንም ምክር ተመልክተሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያኽል ማስጨነቅህ አግባብ ነውን? አንተ ራስህ የፈጠርከውን ሰው መናቅ ይገባሃልን? የክፉ ሰዎችስ ሤራ ደስ ያሰኝሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የኃጥአንንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? |
“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”
እነሆ፥ እግዚአብሔር የዋሁን ሰው አይጥለውም፥ የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም። የዝንጉዎችንም መባ አይቀበልም።