ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ኤርምያስ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃናቱንም በመንገድ፤ ጐልማሶቹንም በአደባባዮቻችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመስኮቶቻችን ወደ ሀገራችን ገብቶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞት በመስኮቶቻችን ገብቷል፤ ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቋል፤ ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞት በየመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ በየቤተ መንግሥታችንም ውስጥ ገብቷል፤ ልጆችን በየመንገዱ፥ ጐልማሶችንም በየአደባባዩ ቀሥፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። |
ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ሕዝቤንም ወደ ዳርቻ ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ስለ ኀጢአታቸው አጥፍቻቸዋለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፤ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፤ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፤ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፤ ጐልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ቅሬታ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ብላቴናንና የሚጠባ ሕፃንን ከመካከላችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?
ስለዚህ ቍጣዬን መላሁባቸው፤ ታገሥሁ፤ ፈጽሜም አላጠፋኋቸውም፤ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጐልማሶችም ጉባኤ ላይ መዓቴን በአንድነት አፈስስባቸዋለሁ፤ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳድራለሁ፤ አባቶችና ልጆችም በአንድነት ይታመማሉ፤ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።