እግዚአብሔርም አለው፥ “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ እንደ ጸሎትህም ሁሉ አደረግሁልህ፤ ለዘለዓለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖችና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።
ኤርምያስ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥታችሁም ስሜ በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ብትቆሙ፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ ከማድረግ ተለይተናል ብትሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሜ ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ ትቆሙና “ደኅና ነን” እያላችሁ እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፦ እነዚህን አስጸያፊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለማድረግ ‘እኛ ድነናል’ አላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምጠላውን ይህን ሁሉ ነገር ከፈጸማችሁ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሴ መጥታችሁ በፊቴ በመቆም ‘እኛ ከጥፋት ድነናል!’ ትላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ። |
እግዚአብሔርም አለው፥ “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ እንደ ጸሎትህም ሁሉ አደረግሁልህ፤ ለዘለዓለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖችና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም፥ “ስሜ በኢየሩሳሌም ለዘለዓለም ይኖራል” ባለው በእግዚአብሔር ቤት የጣዖት መሠዊያዎችን ሠራ።
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ ይህን ስሙ።
እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዓመተ ኅድገትን በማድረግ በዐይኔ ፊት ቅን የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር፤ ስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።
በውኑ በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፥ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፥ የአለቆቻቸውንም ክፋት የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?።
ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት፥ እናንተም በምትተማመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ እንዲሁ አደርጋለሁ።
የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉ ነገርን ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።
እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ኀጢአታችሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱሱን ስሜንም ከእንግዲህ ወዲህ በኀጢአታችሁና በመባችሁ አታርክሱ።
እነርሱም በጥል ያደርጉብሻል፤ የደከምሽበትንም ሁሉ ይወስዳሉ፤ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፤ የግልሙትናሽንም ነውር፥ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽንም ሁሉ ይገልጣሉ።
አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ዝሙታቸውንም ወድደዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና።
ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ እንደዚህ አደረጉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም።
ሰውን እንደሚያደቡ ወንበዴዎች፥ እንዲሁ ካህናት በሴኬም መንገድ ላይ አድብተው ይገድላሉ፤ ዐመፅንም ያደርጋሉ።
ሕጉን በውጭ አነበባችሁ፤ የታመነም አላችሁት፤ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ጌታችን ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት፤ አይሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋሲካውን በግ ሳይበሉ እንዳይረክሱ ወደ ፍርድ አደባባይ አልገቡም።