ኤርምያስ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ወይንን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ይቃርሙአቸዋል፤ እጅህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእስራኤል የተረፉትን የወይን ዘለላን እንደሚለቅም ሰው ልቀሙ፤ መላልሳችሁ ወይንን እንደሚለቅም ሰው እጃችሁን በቅርንጫፎቹ ላይ ዘርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ወይኑን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ፈጽሞ ይቃርሙአቸዋል፥ እጅህንም እንደ ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ። |
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል።
ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተዉልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚያጠፉት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?
በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።