Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ የያዘውን፣ “ዘለላው ስለ በሰለ፣ ስለታም ማጭድህን ያዝና በምድር ላይ ያሉትን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን “ዘለላዎቹ በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቁረጥ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተጣራ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለ በሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድ! የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቈርጠህ ሰብስብ!” በማለት ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 14:18
7 Referencias Cruzadas  

መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”


ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል።”


ከመሰዊያውም “አዎን፤ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።


ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos