La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 52:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከናስ ያሠራቸው፦ ሁለቱ ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፣ ከሥሩ ያሉት ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችና ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡ ሰሎሞንም ለጌታ ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኩሬ፥ ከኩሬውና ከውኃ ማመላለሻ ፉርጎዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ከናስ ለተሠረሩ ዕቃዎች ሁሉ መመዘኛ ሚዛን አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ሁለቱን ምሰሶዎች፥ አንዱን ገንዳ፥ ዐሥራ ሁለት በኰርማ ቅርጽ ከነሐስ የተሠሩትን የገንዳ ማስቀመጫዎች፥ ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ አሠርቶአቸው የነበሩትን ተሽከርካሪ መቆሚያዎችን ሁሉ ወሰደ። እነዚህ ዕቃዎች የተሠሩበት ነሐስ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሊመዘን አልተቻለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን አሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፥ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 52:20
6 Referencias Cruzadas  

ኩሬ​ውም በዐ​ሥራ ሁለት በሬ​ዎች ምስል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስ​ቱም ወደ ምዕ​ራብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስ​ቱም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ኩሬ​ውም በላ​ያ​ቸው ነበረ፤ የሁ​ሉም ጀር​ባ​ቸው በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።


ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዓም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም ዕቃ​ዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።


ሰሎ​ሞ​ንም እነ​ዚ​ህን ዕቃ​ዎች ሁሉ እጅግ አብ​ዝቶ ሠራ፤ የና​ሱም ብዛት አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ሩ​ትን የናስ ዐም​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የነ​በ​ሩ​ትን መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችና የና​ሱን ኩሬ ሰባ​በሩ፤ ናሱ​ንም ወደ ባቢ​ሎን ወሰዱ።