Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 52:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከናስ ያሠራቸው፦ ሁለቱ ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፣ ከሥሩ ያሉት ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችና ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ንጉሡ ሰሎሞንም ለጌታ ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኩሬ፥ ከኩሬውና ከውኃ ማመላለሻ ፉርጎዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ከናስ ለተሠረሩ ዕቃዎች ሁሉ መመዘኛ ሚዛን አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እንዲሁም ሁለቱን ምሰሶዎች፥ አንዱን ገንዳ፥ ዐሥራ ሁለት በኰርማ ቅርጽ ከነሐስ የተሠሩትን የገንዳ ማስቀመጫዎች፥ ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ አሠርቶአቸው የነበሩትን ተሽከርካሪ መቆሚያዎችን ሁሉ ወሰደ። እነዚህ ዕቃዎች የተሠሩበት ነሐስ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሊመዘን አልተቻለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን አሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፥ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 52:20
6 Referencias Cruzadas  

ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር።


ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።


ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ ብሎ ከናስ ያሠራቸው ሁለት ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፤ ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።


“ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።


እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለ ሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።


ባቢሎናውያን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የናስ ዐምዶች፣ ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ከናስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ሰባበሩ፤ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos