ናቡከደነፆርም ከእግዚአብሔር ቤት ዕቃ አያሌውን አውጥቶ ወደ ባቢሎን ወሰደ፤ በባቢሎንም በጣዖቱ ቤት ውስጥ አኖረው።
ኤርምያስ 51:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋታለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርስዋ አይሰበሰቡም፤ የባቢሎንም ቅጥሮች ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤልን በባቢሎን ውስጥ እቀጣለሁ፤ የዋጠውን አስተፋዋለሁ፤ ሕዝቦች ከእንግዲህ ወደ እርሱ አይጐርፉም፤ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይነጉዱም፥ የባቢሎንም ቅጥር ወድቆአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ጣዖት የሆነውን ቤልን እቀጣለሁ፤ የተሰረቁ ዕቃዎቹንም ከእጁ አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህም አሕዛብ አይሰግዱለትም።” “የባቢሎን ቅጽሮች ወድቀዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፥ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል። |
ናቡከደነፆርም ከእግዚአብሔር ቤት ዕቃ አያሌውን አውጥቶ ወደ ባቢሎን ወሰደ፤ በባቢሎንም በጣዖቱ ቤት ውስጥ አኖረው።
በኋላ ዘመን እንዲህ ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ቤት በተራሮች ራስ ላይ ይታያል፤ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመጣሉ።
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
“ለአሕዛብ ተናገሩ፤ አውሩም፤ ዓላማውንም አንሡ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮዳክ ፈራች፤ ምስሎችዋም አፈሩ፤ ጣዖታቷም ደነገጡ፤ በሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎንን ምስሎች የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፤ ምድርዋም ሁሉ ትደርቃለች፤ ተዋግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ረጃጅሞች በሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሕዝቡ ለከንቱ ይደክማሉ፤ አሕዛብም በመጀመሪያ በእሳት ያልቃሉ።”