ኤርምያስ 51:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማይቀመጥበት፥ የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ ዝርም የማይልባቸው፣ ደረቅና ምድረ በዳ፣ ባድማ ምድርም ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞቹ ውሃ የማይገኝባቸውና ማንም ሊኖርባቸውም ሆነ ሊተላለፍባቸው የማይችል ምድረ በዳ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ። |
ለዘለዓለም የሚቀመጥባት አይገኝም፤ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ሰው አይኖርባትም፤ ዓረባውያንም በእርሷ አያልፉም፤ እረኞችም በውስጥዋ አያርፉም።
ስለዚህ ምክንያት ጥፋት ይመጣብሻል፤ ጥልቀቱን አታውቂም፤ በውስጡም ትወድቂያለሽ፤ ጕስቁልና ይመጣብሻል፤ ማምለጥም አይቻልሽም፤ ሞት ድንገት ይመጣብሻል፤ አታውቂምም።
እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፤ እነሆ በአሕዛብ መካከል ኋለኛዪቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረሀም ትሆናለች።
ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር ዐሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች፤ ታመመችም።
አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተናግረሃል በል።