ኤርምያስ 51:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ፤ በሞገዱም ብዛት ተከደነች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕር በባቢሎን ላይ ይወጣል፤ ሞገዱም እየተመመ ይሸፍናታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕሩ በባቢሎን ላይ ወጥቶባታል በሚናወጠውም ሞገዱ ተሸፍናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ጠላቶች እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ወጥተው ከተማይቱን አጥለቀለቋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ በሞገዱም ብዛት ተከደነች። |
ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ ሀገር ከምድረ በዳ ይመጣል።
እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርስዋም ሞገዱ እንደ ብዙ ውኃዎች የሚተመውን ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ የድምፃቸው ጩኸት ተሰምቶአል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን አወጣብሻለሁ።
“በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ።