ኤርምያስ 50:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ትዕቢተኛ ሆይ!፥ ትደክሚያለሽ፤ ትወድቂያለሽም፤ የሚያነሳሽም የለም፤ በዛፎችሽ ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያሽ ያለውንም ሁሉ ትበላለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤ የሚያነሣውም የለም፤ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣ በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ወድቆአ የሚያነሣውም ማንም የለም፤ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ትዕቢተኛይቱ ተሰናክለሽ ትወድቂአለሽ፤ ደግፎ የሚያነሣሽም አይኖርም፤ ከተሞችሽን በእሳት አቃጥላለሁ፤ በዙሪያሽም ያለው ነገር ሁሉ ይደመሰሳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ይወድቃል የሚያነሣውም የለም፥ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች። |
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ከአንተም ለማዕዘን የሚሆን ድንጋይንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይን አይወስዱም፤ ለዘለዓለምም አጠፋሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
በራባ ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በጦርነት ቀን በጩኸት መሠረቶችዋን ትበላለች፤ በፍጻሜዋም ቀን ትናወጣለች።
በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።