ኤርምያስ 50:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቢሎን ሆይ! በመከራው ተይዘሽ ጠፋሽ፤ አንቺም ይህ እንደመጣብሽ አላወቅሽም፤ እግዚአብሔርን ተቃውመሽዋልና ተገኝተሻል፤ ተይዘሽማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ ተገኘሽ፤ ተያዝሽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎን ሆይ! በራስሽ ላይ ባጠመድሽው ወጥመድ ሳታውቂው ተያዝሽበት፤ ተይዘሽ የተጋለጥሽውም እግዚአብሔርን ስለ ተዳፈርሽ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል። |
“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን?
እርስዋን በምጐበኝበት ዓመት በሞአብ ላይ ይህን አመጣለሁ፤ በፍርሀት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጕድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ ይላል እግዚአብሔር።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹሞችዋን፥ ኀያላኖችዋንም አሰክራለሁ፤ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።