ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
ኤርምያስ 48:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፍረስና ታላቅ ጥፋት፥ የሚል የጩኸት ድምፅ ከሖሮናይም ተሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሖሮናይም ላይ በሚደርሰው ውድመትና ጥፋት የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ። |
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
ያም ሰው እግዚአብሔር በቍጣው እንደ ገለበጣቸው፥ ይቅርም እንደ አላላቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን፥ በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰሜን ይነሣል፥ የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፤ በሀገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማዪቱና በሚኖሩባትም ላይ ይጐርፋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና።