Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 48:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በሖሮናይም ላይ በሚደርሰው ውድመትና ጥፋት የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 መፍረስና ታላቅ ጥፋት፥ የሚል የጩኸት ድምፅ ከሖሮናይም ተሰማ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መፍ​ረ​ስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩ​ኸት ቃል ከሖ​ሮ​ና​ይም ተሰማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:3
12 Referencias Cruzadas  

የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል።


ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።


በሞአብ ጠረፎች በየስፍራው ጩኸት ይሰማል፤ ጩኸቱም እስከ ኤግላይምና እስከ ብኤርኤሊም ደርሶአል።


ስለ ሞቱት ሕዝቦቼ በመረረ ሁኔታ አለቅስላቸው ዘንድ ተዉኝ፤ አታጽናኑኝ።


ያ ሰው፥ እግዚአብሔር ያለምሕረት እንደ ደመሰሳቸው ከተሞች ሆኖ ይቅር፤ በማለዳ የዋይታ ጩኸት ይስማ፤ በቀትርም በጦርነት ወሬ ይሸበር።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።


“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።


“ሞአብ ተደምስሳለች፤ ልጆችዋም ጩኸትን ያሰማሉ።


ወደ ሉሒት ሲወጡ ምርር ብለው እያለቀሱ ይወጣሉ፤ ወደ ሖሮናይም ቊልቊለት ሲወርዱ በውድመቱ ምክንያት የጭንቀት ድምፅ ያሰማሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከባቢሎን ጩኸት፥ ከከለዳውያን ምድርም የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos