ኤርምያስ 48:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠንካራውም ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትረ መንግሥት፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ!፥ ብላችሁ አልቅሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዝናዋን የምታውቁና በአቅራቢያዋ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ‘የሥልጣን ምልክት የሆነው የተከበረው ኀይልዋ፥ በትረ መንግሥትዋ እንዴት ተሰበረ’ በማለት ዋይ! ብላችሁ አልቅሱላት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትር፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። |
የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
እንዴት ተለወጠች! ከእፍረትም የተነሣ ሞአብ ጀርባዋን እንዴት መለሰች! ሞአብም በዙሪያዋ ላሉት ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ትሆናለች።