ኤርምያስ 46:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊትም በኀይል ይዘምቱባታልና፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታልና ድምፅዋ እንደምትሸሽ እባብ ይተማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ ግብጽ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣ መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጠላቶችዋ በኃይል ዘምተው እንደ እንጨት ቈራጮች በምሳር ይመጡባታልና በደረቱ እንደሚሽሎኮሎክ እባብ ድምፅ ታሰማለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠላት ሠራዊት ኀይል ሲቃረብ ግብጽ እንደ እባብ የፉጨት ድምፅ እያሰማች ትሸሻለች፤ ሰዎች ጥቅጥቅ ያለውን ደን እንደሚመነጥሩ በመጥረቢያ አደጋ ይጥሉባታል። የሰዎቻቸው ብዛት በቊጥር አይደረስበትም፤ የወታደሮቻቸውም ብዛት ከአንበጣ ሠራዊት ይበልጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሠራዊትም ጋር ይሄዳሉና ድምፅ እንደ እባብ ይተምማል፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታል። |
“በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።”
ነገርሽም በምድር ውስጥ ይሰጥማል፤ ቃልሽም ከምድር በታች እንደሚናገር ይሆናል፤ ትደክሚያለሽ፤ ቃልሽም በምድር ውስጥ ዝቅ ይላል።
አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
ሊቈጠሩ የማይችሉ የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከአንበጣ ይልቅ በዝተዋልና፥ ቍጥርም የላቸውምና።
አለቆቹም “አዳንናችሁ፤ ለማኅበሩም እንጨት ትቈርጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደብናችሁ” አሉአቸው። አለቆቹም እንዲሁ አዘዙአቸው።