ኤርምያስ 45:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፦ እግዚአብሔር በሕማሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም ብለሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ፣ ‘እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም’ ብለሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ፦ ‘ጌታ በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም’ ብለሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኝ ምንም ዕረፍት ሳይኖረኝ በመቃተት ደክሜአለሁና ወዮልኝ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ፦ እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም ብለሃል። |
ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ።
ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥ ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኀጢአቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረምኸኝ እነርሱን ቃርማቸው።