ኤርምያስ 44:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስቶቻቸውም ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፥ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግብፅም ምድር በጳትሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ መለሱለት፤ እንዲህም አሉ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ወንዶች ሁሉና በዚያ የነበሩት ሴቶች ሁሉ ይህም ማለት በሰሜንና በደቡብ ግብጽ የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ እንዲህ አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቶቻቸውም ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ በዚያም ቆመው የነበሩ ሴቶች ሁሉ፥ በግብጽ ምድር በጳትሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ መለሱለት እንዲህም አሉ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ መሆናቸውን የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፥ በግብጽ ደቡባዊ ክፍል የሚኖሩት እስራኤላውያንና በዚያ ቆመው የነበሩት ሴቶች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው በመቅረብ እንዲህ አሉኝ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስቶቻቸውም ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግብጽ ምድር በጳትሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ መለሱለት እንዲህም አሉ፦ |
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኀጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፤ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
ስለዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፤ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌም ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ የሚሆነውን ከመሆኑ በፊት ነገርሁህ፤ አስረዳሁህም፤
በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ፥ በሜምፎስም፥ በፋቱራም ሀገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት፥ የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ምስልዋን ለማበጀት እንጎቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?”
ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፥ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
የግብፅንም ምርኮ እመልሳለሁ፤ ወደ ተወለዱባትም ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ፤ በዚያም የተዋረደች መንግሥት ይሆናሉ።
ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥