Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 44:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እኛስ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ባጠ​ን​ን​ላት፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን ባፈ​ሰ​ስ​ን​ላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎ​ቻ​ችን ምስ​ል​ዋን ለማ​በ​ጀት እን​ጎቻ አድ​ር​ገ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን? የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን?”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሴቶቹም፣ “ለሰማይዋ ንግሥት በምናጥንበትና የመጠጥ ቍርባን በምናፈስስበት ጊዜ፣ በምስሏ ዕንጐቻ ስንጋግርና የመጠጥ ቍርባን ስናፈስስላት ባሎቻችን አያውቁም ነበርን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቁርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ፈቃድ ምስልዋ ያለበት እንጐቻ አድርገንላታልን? የመጠጥንስ ቁርባን አፍስሰንላታልን?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሴቶችም ጨምረው ሲናገሩ፥ “በሰማይ ንግሥት እንጎቻ በምንጋግርበት ጊዜ፥ ለእርስዋ መሥዋዕትና የወይን ጠጅ መባ በምናቀርብበት ጊዜ፥ ከባሎቻችን ተለይተን ያደረግነው ነገር አልነበረም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 44:19
14 Referencias Cruzadas  

ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እን​ጎቻ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን እን​ዲ​ያ​ፈ​ስሱ ልጆች እን​ጨት ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ አባ​ቶ​ችም እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ ሴቶ​ችም ዱቄት ይለ​ው​ሳሉ።


ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ማጠ​ና​ቸ​ውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፥ በዚ​ያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግ​ብ​ፅም ምድር በጳ​ት​ሮስ የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤ​ር​ም​ያስ መለ​ሱ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አሉ፦


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


ሌሎች ሠራ​ዊ​ትን እና​መ​ጣ​ል​ሃ​ለን፤ አን​ተም ቀድሞ በሞ​ቱ​ብህ ሠራ​ዊት ምትክ ሹም፤ ፈረ​ሱን በፈ​ረስ ፋንታ፥ ሰረ​ገ​ላ​ውን በሰ​ረ​ገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜ​ዳ​ውም እን​ዋ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፤ ድልም እና​ደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለን።” እር​ሱም ምክ​ራ​ቸ​ውን ሰማ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።


በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል።


ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ለመ​ለ​ሱ​ለት ሕዝብ ሁሉ፦ ለወ​ን​ዶ​ቹና ለሴ​ቶቹ፥ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አለ፦


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ አይ​ጸ​ኑም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይቅር ይላ​ታል።


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios