ኤርምያስ 38:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ሲል የተናገረውን ቃል የናታን ልጅ ሰፋንያስ፥ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፥ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፥ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ ለሕዝቡ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ሰፋጥያስ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሰሌምያ ልጅ ዮካል እንዲሁም የመልክያ ልጅ ጳስኮር ሰሙ፤ ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃላት የማታን ልጅ ስፋጥያስ፥ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፥ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፥ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማታን ልጅ ሰፋጥያ፥ የፓሽሑር ልጅ ገዳልያ፥ የሼሌምያ ልጅ የሁካልና የመልክያ ልጅ ፓሽሑር እግዚአብሔር የነገረኝን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ማስተማሬን ሰሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ፥ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፥ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፥ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። |
የመልክያ ልጅ፥ የጳስኮር ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ አዳያ፤ የኤሜር ልጅ የምስልሞት ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ፥ የኤሕዜራ ልጅ፥ የዓዴኤል ልጅ መዕሣይ፤
የእግዚአብሔርንም የቤቱን ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሃያ ሁለት የመልክያ ልጅ፥ የፋስኩር ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የአማሴ ልጅ፥ የፈላልያ ልጅ፥ የይሮሖም ልጅ ዓዳያ፥
“በኢየሱስ ስም ለማንም እንዳታስተምሩ ከልክለናችሁ አልነበረምን? እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመጡብን ዘንድ ትሻላችሁን?” አላቸው።