ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።”
ኤርምያስ 37:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አቤቱ ንጉሥ ሆይ! ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ፤ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሓፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እባክህ አድምጠኝ፤ ልመናዬን በፊትህ ላቅርብ፤ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሓፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እንድትሰማኝ አሁን እለምንሃለሁ፤ እባክህ፥ ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ፤ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! እንድታዳምጠኝና የምጠይቅህን እንድትፈጽምልኝ እለምንሃለሁ፤ ይኸውም እስር ቤት ወደ ሆነው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ፤ ወደዚያ ከመለስከኝ በእርግጥ እሞታለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ ጌታዬ ሆይ፥ እንድትሰማኝ አሁን እለምንሃለሁ፥ እባክህ፥ ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ፥ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ። |
ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።”
እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትደርስ ይሆናል፤ ሁሉም ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”
እንዲህም አሉት፥ “እባክህ ልመናችን በፊትህ ትድረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነዚህም ቅሬታዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ ዐይኖችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና።