ዳዊትም፥ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም ስለ አባቱ ያጽናኑት ዘንድ ብላቴኖቹን ላከ፤ የዳዊትም ብላቴኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።
ኤርምያስ 37:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሆነ፥ አገልጋዮቹ፥ የሀገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እርሱም ሆነ መኳንንቱ የምድሪቱም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት የተነገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነቢዩ በኤርምያስም በኩል የተናገረውን የጌታን ቃላት እርሱም ሆነ ባርያዎቹ የአገሩም ሕዝብ አልሰሙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስም ሆነ መኳንንቱ ወይም ሕዝቡ እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት ለተናገረው ቃል ታዛዦች አልሆኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሆነ ባሪያዎቹ የአገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። |
ዳዊትም፥ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም ስለ አባቱ ያጽናኑት ዘንድ ብላቴኖቹን ላከ፤ የዳዊትም ብላቴኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።
በእጁም ሥራ ያስቈጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ስላደረገው ክፋት ሁሉ እርሱንም ስለ ገደለው፥ የእግዚአብሔር ቃል በባኦስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፋ ትሰጣለች፤ ይይዛታል፤ በእሳትም ያቃጥላታል።
እኔም ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድንኳን አስቀምጥሃለሁ።