ኤርምያስ 37:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ይኖር ዘንድ ወደ ብንያም ሀገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ለመካፈል፣ ከኢየሩሳሌም ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ተነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ከዚያ ለመቀበል ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ከቤተሰቤ የሚደርሰኝን የርስት ክፍያ ለመቀበል ወደ ብንያም ግዛት ለመሄድ ከኢየሩሳሌም ተነሣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን እድል ፈንታ ከዚያ ይቀበል ዘንድ ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። |
እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል።
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።