Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 37:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ከዚያ ለመቀበል ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ለመካፈል፣ ከኢየሩሳሌም ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ተነሣ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እኔም ከቤተሰቤ የሚደርሰኝን የርስት ክፍያ ለመቀበል ወደ ብንያም ግዛት ለመሄድ ከኢየሩሳሌም ተነሣሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ኤር​ም​ያስ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ይኖር ዘንድ ወደ ብን​ያም ሀገር ሊሄድ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን እድል ፈንታ ከዚያ ይቀበል ዘንድ ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 37:12
11 Referencias Cruzadas  

በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃላት።


ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።


ከዚያች ከተማ ቢያሳድዱአችሁ ወደ ሌላዪቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞች አትጨርሱም።


እኔም፦ “እንደ እኔ ያለ ሰው ይሸሻልን? እንደ እኔ ያለ ነፍሱን ሊያድን ወደ መቅደስ የገባ ማን አለ? አልገባም” አልሁ።


እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።


እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ። በድንገትም ጌታ “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው።


የፈርዖንም ሠራዊት ከመቃረቡ የተነሣ የከለዳውያን ሠራዊት ከኢየሩሳሌም ተመልሶ በነበረ ጊዜ፥


በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios