ኤርምያስ 36:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም ዐዋጅ ነገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሆነው ኢዮአቄም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች የመጡት ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ጾም ዐወጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር፥ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ሕዝብ ሁሉ በጌታ ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብና ከይሁዳ ከተሞች የመጡት ሕዝብ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ለማግኘት የጾም ጊዜ አወጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ። |
በዚህም ወር በሃያ አራተኛው ቀን የእስራኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብሰው፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው ተሰበሰቡ።
እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመተ መንግሥት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ።
አንተ ግን ገብተህ ከአፌ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንብብ፤ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።
ጾምን ቀድሱ፤ ምህላንም ዐውጁ፤ ሽማግሌዎቹንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ጩኹ።
“በዚህ በሰባተኛው ወር ዐሥረኛዋ ቀን የማስተስረያ ቀን ናት፤ ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለቀሱም፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትንና የደኅንነት መሥዋዕትን አቀረቡ።
እነርሱም ወደ መሴፋ ተሰበሰቡ፤ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አፈሰሱ፤ በዚያም ቀን ጾሙ፤ በዚያም፥ “በእግዚአብሔር ፊት በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በመሴፋ ፈረደ።