ኤርምያስ 36:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ልጅ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፥ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከእርሱም በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይኖረውም፥ ሬሳውም በቀን ለፀሐይ ሐሩርና በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮአቄም ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ይህ ነው፦ ‘ከዘርህ በዳዊት መንግሥት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከቶ አይኖርም፤ ሬሳህም የትም ተጥሎ ለቀን ፀሐይ ሐሩርና ለሌሊት ቊር የተጋለጠ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ብዙ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል” አልሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።