ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
ኤርምያስ 32:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብፅ ምድር፥ ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፤ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ ታምራትንና ድንቆችን አደረግህ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤልና በሰው ልጆች ሁሉ መካከል እንደዚያው እያደረግህ ዛሬም ስምህ ገናና ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር፥ እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ በዚህም እስከ ዛሬዋ ቀን ስምህን አጽንተሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀድሞ ጊዜ በግብጽ ምድር ተአምራትንና አስደናቂ ነገሮችን አደረግህ፤ እስከ አሁንም ድረስ እነዚያን ድንቅ ሥራዎች በእስራኤል ሕዝብና በሌሎች ሰዎች መካከል ከማድረግ አልተቈጠብክም፤ ከዚህም የተነሣ በሁሉ ስፍራ ስምህ ገኗል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል። |
ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
አንተ እግዚአብሔር ከግብፅ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ ታላቅና የከበረ ስምን ለአንተ ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም።
እንደ ታበዩባቸውም ዐውቀህ ነበርና በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ፥ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትንና ተአምራትን አሳየህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስምህን አስጠራህ።
ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፤ በባሕሩም መካከል በደረቅ ዐለፉ፤ የተከተሉአቸውን ግን ድንጋይ በጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።
በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፤ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስምን ታደርግ ዘንድ ሕዝብህን መራህ።
መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ለስም፥ ለመመኪያና ለክብር ሕዝብ ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም።”
አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥
አምላክህ እግዚአብሔር ዓይንህ እያየች፥ ታላቅ መቅሠፍትን፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ የጸናችውንም እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።