ኤርምያስ 29:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርስዋ ሰላም፥ ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ሀገር ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተማርካችሁ ለሄዳችሁባት ከተማ ሰላምና ብልጽግናን እሹ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸልዩላት፤ ምክንያቱም እርሷ ብትበለጽግ እናንተም ትበለጽጋላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሷ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና እናንትን አስማርኬ ያፈለስኩባትን ከተማ ሰላም ፈልጉ፥ ስለ እርሷም ወደ ጌታ ጸልዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተማርካችሁ ሄዳችሁ እንድትኖሩባቸው ላደረግኋቸው ከተሞችም ዕድገት መልካም ነገርን ተመኙ፤ ስለ እነርሱም መልካም ኑሮ ወደ እኔ ጸልዩ፤ እነርሱ መልካም ኑሮ ቢኖሩ እናንተም መልካም ኑሮን ትኖራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ። |
በንጉሡ መንግሥትና በልጆቹ ላይ ቍጣ እንዳይሆን፥ የሰማይ አምላክ ያዘዘው ሁሉ ይደረግ፤ ለሰማይ አምላክ ቤት የታዘዘውንም እንዳታቋርጡ ተጠንቀቁ።
አለቆቹም ንጉሡን፥ “ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚያች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ፥ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፤ ወደ ሀገሮችም እበትናቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ በመጡባቸው ሀገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።
ሰው ሁሉ በበላይ ላሉ ባለሥልጣኖች ይገዛ፤ ከእግዚአብሔር ከአልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።