እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
ኤርምያስ 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች፣ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኢየሩሳሌም፥ በቤተ መቅደሱና በቤተ መንግሥቱ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የእስራኤል አምላክ የሆንኩ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምናገረውን ቃል ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ |
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንም ቤት መዝገብ፥ የአለቆቹንም ቤት መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሲሳብሳር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞች ጋር ወሰደ።
ንጉሡ ቂሮስም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወስዶ በአምላኩ ቤት ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃዎች አወጣ።
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
የዚችንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪቷንም ሁሉ፥ ክብርዋንም ሁሉ፥ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይበዘብዙአቸዋል፤ ይዘውም ወደ ባቢሎን ያስገቡአቸዋል።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ፥
ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ እስከምጐበኛቸው ቀን ድረስ በዚያ ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በዚያን ጊዜም ትወጣላችሁ፤ ወደዚህም ስፍራ ትመለሳላችሁ።”
ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።