Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 27:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች፣ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “በኢየሩሳሌም፥ በቤተ መቅደሱና በቤተ መንግሥቱ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የእስራኤል አምላክ የሆንኩ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምናገረውን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 27:21
9 Referencias Cruzadas  

‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤


የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።


የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሼሽባጻር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞቹ ጋር ወሰደ።


ንጉሡ ቂሮስም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወስዶ በአማልክቱ ቤት ያኖራቸውን የጌታን ቤት ዕቃዎች አወጣ።


እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል ጌታ።


የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያመጡአቸዋል።


እነዚህም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን መሳፍንት ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ያልወሰዳቸው ዕቃዎች ነበሩ፤


ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፥ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቆያሉ፥ ይላል ጌታ፤ ከዚያም በኋላ አውጥቼአቸው ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ።”


ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፥ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos