ኤርምያስ 26:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢዮአቄም ሰዎችን ወደ ግብፅ ላከ፤ የአክቦርን ልጅ ኤልናታንን፥ ሌሎችንም ሰዎች ከርሱ ጋራ ወደ ግብፅ ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንንና ከርሱም ጋራ ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦር ልጅ ኤልናታንና ሌሎችም ሰዎች ወደ ግብጽ ወርደው ኡሪያን ይዘው እንዲመጡ አዘዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፥ |
ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክዩንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሓፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓስያን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦
እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
ኤርምያስም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው፦
ወደ ንጉሡም ቤት ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ እነሆም አለቆቹ ሁሉ፥ ጸሓፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፥ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ኤርምያስንም ከግዞት ቤቱ አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
በፊታቸውም ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎችና የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያንዳንዱ በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።