በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው፥ ወደ መረጥሃትም ከተማ፥ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥
ኤርምያስ 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና ሕዝቤ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ጌታ እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና፥ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ። ከዚያ በኋላም በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ፥ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። |
በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው፥ ወደ መረጥሃትም ከተማ፥ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥
ቃሌን በአፍሽ አደርጋለሁ፤ ሰማይን በዘረጋሁበትና ምድርን በመሠረትሁበት በእጄ ጥላ እጋርድሻለሁ፤ ጽዮንንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላታለሁ።
ከግብፅ ሀገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁትን፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ” ያልሁትን ቃሌን ስሙ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
ስለዚህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአሕዛብ ዘንድ እቀበላቸዋለሁ፤ ከበተንሁባቸውም ሀገሮች እሰበስባቸዋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ይኸውም የእስራኤል ቤት ደግሞ ከእኔ ርቀው እንዳይስቱ፥ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳይረክሱ ነው፤ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው፥ በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፤ ኀጢአትም ከሠሩባት ዐመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ፤ አነጻቸውማለሁ፤ ሕዝብም ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
የኀጢአት ተገዦች ስትሆኑ ምሳሌነቱ ለተሰጣችሁ ለምትማሩት ትምህርት ታዝዛችኋልና እግዚአብሔር ይመስገን።
አሁን ግን፥ በሰማያት ያለችውን የምትበልጠውን ሀገር ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእነርሱ አያፍርም፤ ተስፋ ያደረጉአትን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋልና።
ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና ምስሎቻቸውን ከመካከላችሁ አርቁ፤ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” ብሎ ተናገራቸው።