La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ይህ ሰው ልጆቹን ሁሉ አጥቶ ኑሮው የማይሳካለት እንዲሆን ተፈርዶበታል፤ የዳዊትን ዙፋን ለመውረስ በይሁዳ የሚነግሡ ዘሮች አይተርፉለትም ብለሽ መዝግቢ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 22:30
11 Referencias Cruzadas  

ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሚ​ራ​ራ​ለት የለም፤ ቤቱ ከሰ​ማይ በታች አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።


እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።


በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


ስለ​ዚ​ህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ አይ​ኖ​ር​ለ​ትም፥ ሬሳ​ውም በቀን ለት​ኩ​ሳት፥ በሌ​ሊ​ትም ለው​ርጭ ይጣ​ላል።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በፊቱ ገደ​ላ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ሁሉ ደግሞ በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው።