እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እናንተም አለቆች ሆይ፥ አድምጡ፤ ምድርና በውስጥዋም ያሉ፥ ዓለምና በውስጥዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።
ኤርምያስ 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ሆይ፤ አንቺ ምድር፣ አንቺ ምድር፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የጌታን ቃል ስሚ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር፥ ምድር፥ ምድር ሆይ! እግዚአብሔር የሚለውን ቃል እነሆ አድምጪ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ። |
እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እናንተም አለቆች ሆይ፥ አድምጡ፤ ምድርና በውስጥዋም ያሉ፥ ዓለምና በውስጥዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።
ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላልሰሙ፥ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ እኔንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
አሁንም ይህችን መዝሙር ለእናንተ ጻፉ፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተምሩአቸው፤ ይህችም መዝሙር በእስራኤል ላይ ምስክር ትሆንልኝ ዘንድ በአፋቸው አድርጓት።
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።