በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
ኤርምያስ 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በተማረከበት ሀገር ይሞታል፤ እንግዲህም ወዲህ ሀገሩን አያይም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተማርኮ በሄደበት አገር ይሞታል እንጂ ይህችን ምድር ዳግመኛ አያይም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተማረከባት አገር በዚያ ይሞታል እንጂ፤ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ተማርኮ በተወሰደበት አገር ስለሚሞት ዳግመኛ ተመልሶ ይህችን ምድር አያይም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህም ወደዚህ አይመለስም፥ በተማረከባት አገር ይሞታል እንጂ፥ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም። |
በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
ፈርዖን ኒካዑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ዮአክስንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈለሰው፤ በዚያም ሞተ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት!
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።