ዓመቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ የአባቱን የኢዮአቄምን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ኤርምያስ 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚችንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪቷንም ሁሉ፥ ክብርዋንም ሁሉ፥ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይበዘብዙአቸዋል፤ ይዘውም ወደ ባቢሎን ያስገቡአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያመጡአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ጠላቶቻቸው የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ እንዲዘርፉት፥ ያካበተችውንም ሀብትና ንብረት አጋብሰው የይሁዳን ነገሥታት የሀብት መዛግብት እንኳ ሳይቀር ጠራርገው ወደ ባቢሎን እንዲወስዱት አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያፈልሱአቸዋል። |
ዓመቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ የአባቱን የኢዮአቄምን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
ወራዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥተዋል፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።
በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ፥ የኮረብታውን መስገጃዎችህንም ስለ ኀጢአትህ በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ።
ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችንን ሥራ፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል።
አሕዛብም መጥተው ይህችን ሀገር ያዟት፤ ይህችም ከተማ ከረኃቡና ከጦሩ የተነሣ በወጓት በከለዳውያን ሰዎች እጅ ወደቀች፤ እንደ ተናገርኸውም ሆነ።
በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመተ መንግሥት በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማዪቱ ተለያየች።
ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።
ዛይ። ኢየሩሳሌም ቀድሞ ወድዳ በሠራችው ሥራ ሁሉ የመከራዋን ወራት አሰበች፤ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ፥ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት፤ በመፍረስዋም ሳቁ።
በመካከሏ ያሉ ነቢያት እንደ አንበሳ ያገሳሉ፤ ይነጥቃሉ፤ ፈጽመውም ይቀማሉ፤ ሰውነትንም ያጠፋሉ፤ መማለጃንም ይቀበላሉ፤ በመካከልዋም መበለቶችዋ ይበዛሉ።
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።