የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።
ኤርምያስ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ፥ የኮረብታውን መስገጃዎችህንም ስለ ኀጢአትህ በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣ በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣ መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ ለብዝበዛ አደርገዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመላ አገራችሁ በፈጸማችሁት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ያላችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም መሠዊያዎቻችሁን ሁሉ በምርኮ ጠላቶቻችሁ እንዲወስዱ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ፥ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ። |
የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
ወራዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥተዋል፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።
የዚችንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪቷንም ሁሉ፥ ክብርዋንም ሁሉ፥ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይበዘብዙአቸዋል፤ ይዘውም ወደ ባቢሎን ያስገቡአቸዋል።
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።
ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።
በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ የምንዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብስሽንም ይገፉሻል፤ የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፤ ዕራቁትሽንም ይተዉሻል፤ ቷረጃለሽም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጉባኤን አመጣባቸዋለሁ፤ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ለእስራኤል ተራሮች የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፤ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በእጅ የተሠሩ የዕንጨት ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፤ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።