ኤርምያስ 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁን ግን ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እነርሱም ያጠምዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ ዐዳኞችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ከየተራራው፣ ከየኰረብታው ሁሉ ከየዐለቱም ስንጣቂ ዐድነው ይይዟቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እልካለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፥ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰድዳለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል። |
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ያገባሉ።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ሀገሯ ሁሉ ሸሽታለች፤ ወደ ዋሻዎች ይገባሉ፥ በዛፍ ሥር ተሸሸጉ፥ በቋጥኝም ላይ ይወጣሉ፤ ከተማዋ ሁሉ ተለቅቃለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው የለም።
እነሆ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሀትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፤ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ወይንን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ይቃርሙአቸዋል፤ እጅህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ።
ጻዴ። ልጆቻችንን ወደ አደባባያችን እንዳይወጡ ከለከልን፤ የምንጠፋበት ጊዜ ደርሷልና ዘመናችን አለቀ፤ የምንጠፋበትም ጊዜ ቀረበ።
ጌታ አግዚአብሔር፥ “እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል” ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።
ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ይሆናል።
በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እመረምራለሁ፣ በአተላቸውም ላይ የሚቀመጡትን፥ በልባቸውም፦ እግዚአብሔር መልካምን አያደርግም፥ ክፉም አያደርግም የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።
አሁንም በተራራው ላይ ሰው ቆቅን እንደሚሻ የእስራኤል ንጉሥ ነፍሴን ለመሻት ወጥቶአልና ደሜ በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አይፍሰስ።”