አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”
ኤርምያስ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአት ሠርተናልና ኃጢአታችን ይመሰክርብናል ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ። |
አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”
ዐመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኀጢአታችንም መስክሮብናልና፥ ዐመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድቅንም አላወቅንምና።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፥ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚያም አመነዘረች።
ስለዚህ ኀጢአታቸው በዝቶአልና፥ የዐመፃቸውም ብዛት ጸንቶአልና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፤ የበረሃም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፤ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
ነገር ግን በመካከላቸው በአሉ፥ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኀጢአታቸው ይደክማሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ይደክማል።
የእስራኤልም ውርደቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፤ በዚህም ሁሉ እግዚአብሔርን አልፈለጉትም።
የምድሩንም ሣር በልቶ ይጨርሳል፤ እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብን ማን ያነሣዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።
በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።
ከነዓናውያንም፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፤ ከምድርም ያጠፉናል፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?”