ኤርምያስ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋሊያዎች ደግሞ በምድረ በዳ ወለዱ፤ ሣርም የለምና ግልገሎቻቸውን ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳች ሣር ባለመኖሩ፣ የሜዳ አጋዘን እንኳ፣ እንደ ወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዋላ ደግሞ በምድረ በዳ ወለደች፥ ሣርም የለምና ግልገልዋን ተወች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣር ካለመገኘቱ የተነሣ፥ አጋዘን እንደ ወለደች ግልገልዋን በሜዳ ላይ ጥላ ትሄዳለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋላ ደግሞ በምድረ በዳ ወለደች፥ ሣርም የለምና ግልገልዋን ተወች። |
እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና።